ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሠራ መኾኑን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ገለጹ።

31

ባሕር ዳር: የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ29ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም 29ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ጠቅላላ ጉባኤ መሪ ቃል እንደሚያመላክተው፡-ቀዳማዊ እመቤቶች የላቀ አመራር በመስጠት፣አፍሪካዊ እሴቶችን በማጎልበት፤ሴቶችን በሁሉም መስክ በመደገፍ ለመሪነት ለማብቃት በትኩረት መሥራት እንዳለብን ያመላክታል ነው ያሉት።

ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ መንግሥት በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ፣ የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

ከቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጽሕፈት ቤታቸው ሴቶችን በኢኮኖሚው ማብቃት ላይ በማተኮር ሦስት ዋና ዋና ሀገር አቀፍ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ ይገኛል ነው ያለሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ያፈነገጠ እና የተዛባ አመለካከት ይዘው ጫካ የገቡ ወገኖችን ምከሩ” አቶ ፍስሃ ደሳለኝ
Next article“ሰላምን የማረጋገጥ ተግባር ቀዳሚ አድርገን የምንሠራበት ጉዳይ ነው” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ