
ባሕር ዳር: የካቲት 10/2017 ዓ.ም(አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ ከዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በመኾን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተናል ብለዋል።
በጉብኝታችን ወቅት ሁለቱ ሀገራት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ በቴክኖሎጂ እና ሌሎች የትብብር መስኮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም አያሌ ዓመታትን የተሻገር ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል።
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጉብኝትም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ትብብር እያደገ ስለመምጣቱ ማሳያ ነው መኾኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!