
ወልድያ: የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በፍላቂት ከተማ በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ በሰሜን ወሎ ዞን ከፍላቂት ገረገራ ከተማ አሥተዳደር እና ከመቄት ወረዳ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር ውይይ እያደረጉ ነው።
ውይይቱን የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሃ ደሳለኝ እና የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር እየመሩት ነው።
በውይይቱ ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የዞን የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!