
ባሕር ዳር: የካቲት 10/2017 ዓ.ም(አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከዞን የግብርና መምሪያ ኀላፊዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አጀበ ስንሸው በ2016/17 የምርት ዘመን 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ ከ169 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት ተችሏል ብለዋል።
የዝናብ አጀማመሩ፣ ስርጭቱ እና አጨራረሱ ለሰብል ልማት ሥራው ጥሩ ነበር ያሉት ምክትል ኀላፊው ምርትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ግብዓቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም ተችሎ እንደነበር አስታውሰዋል።
እንደ ክልል 7 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በማሰራጨት የአርሶ አደሮችን ፍላጎት ማርካት በመቻሉ ከዕቅድ በላይ ምርት ማግኘት ተችሏል ነው ያሉት።
በምርጥ ዘር አቅርቦት በቆሎ፣ ጤፍ እና ስንዴ የራስን ፍጆታ ከማረጋገጥ ባለፈ ለሌሎች ክልሎችም መትረፍ መቻሉን በስኬት አንስተዋል።
ለ2017/18 የመኽር ምርት ለአርሶ አደሮች አስፈላጊውን ግብዓት እና ቴክኖሎጂ ለማቅረብ የበለጠ መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!