
ባሕር ዳር: የካቲት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ተቀብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል።
በታላቅ የለውጥ ጉዞ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሚኖርዎት ጉብኝትና ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን