
ወልድያ: የካቲት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል እና የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በ132 ሚሊዮን ብር የተገነባውን የጋዞ ወረዳ አሥተዳደር ምክር ቤት ቢሮ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ሁለገብ የቢሮ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የተገነባው ሕንፃ ባለ አምስት ወለል ነው። 1 ሺህ 200 ሰው የሚይዝ ከፍተኛ አዳራሽ እና ተጨማሪ አነስተኛ አዳራሾች እንዳሉትም ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን