
ወልድያ: የካቲት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ጋዞ ወረዳ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የእስታይሽ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ግንባታ፣ የማሠልጠኛ ማሽኖች ተከላ፣ በኅብረተሰቡ ተሳትፎ እየተገነባ ያለው የጋዞ ወረዳ ፍርድ ቤት ሕንፃ እና የእስታይሽ ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ ግምባታ በሥራ ኅላፊዎች ተጎብኝተዋል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የልማት ሥራዎቹ ኅብረተሰቡ አካባቢውን የመለወጥ ፍላጎት እንዳለው ያሳዩ ናቸው ብለዋል። በችግር ውስጥ ኾኖ መሥራት እንደሚቻልም ማሳያ እንደኾኑም ገልጸዋል።
መሪ ከምክንያት ነፃ ኾኖ የልማት ሥራን መሥራት እንደሚችል እና ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ ሊሆን እንደሚገባ ጉብኝታችን አረጋግጧል ነው ያሉት።
ከኅብረተሰቡ አቅም በላይ የኾኑ እና ተቋሟቱ የሚጎድላቸውን ነገሮች በቅደም ተከተል እንዲሟሉ ምክር ቤቱ ይከታተላል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን