
ባሕር ዳር፡ የካቲት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሀሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው ተመርጠዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለመሆን ሶስት እጩዎች ከፍተኛ ፉክክር ሲያደርጉ ቆይተዋል።
በዚህም በሥራ ላይ ያሉትን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት ለመተካት በተካሄደው ምርጫ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀመድ አሊ ዩሱፍ 33 ድምፅ በማግኘት ምርጫውን አሸንፈዋል።
በ7 ዙር በተካሄደው ምርጫ እጩ ኾነው የቀረቡት የቀድሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ 21 ድምፅ በማግኘት ሁለተኛ ኾነዋል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ወርቅነህ ገበየሁ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ማሀሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!