ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ።

32

ባሕር ዳር: የካቲት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪን አዴሲና እና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋር ተወያይተዋል።

ከ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ጎን ለጎን ከፕሬዝዳንቶቹ ጋር መወያየታቸውን በኤክስ ገጻቸው ያጋሩት ጠቅላይ ሚኒስተትሩ ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚያደርጉትን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በሚመለከት መምከራቸውን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢንዱስትሪው ውስጥ ቀጣይነት ያለው እድገትን እና የመቋቋም አቅምን ለማጎልበት ትብብርን ስለማሳደግም ተወያይተናልም ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከጋቪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ።
Next articleማሀሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ኾነው ተመረጡ።