“ከዓለም ሀገራት ጋር እኩል ለመጓዝ ለቴክኖሎጂው ዘርፍ ትኩረት መስጠት ይገባል” ሙሳ ፋኪ ማሐመት

43

ባሕር ዳር: የካቲት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከዓለም ሀገራት ጋር እኩል ለመጓዝ ለቴክኖሎጂው ዘርፍ በተለይም ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሐመት ተናገሩ።

ሙሳ ፋኪ መሐመት በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር የቴክኖሎጂው ዘርፍ የተለየ ትኩረትን እንደሚሻ ተናግረዋል።

ጉባዔው ሊተገብረው ያሰበውን ሪፎረም በማስታወስ ይህም የኅብረቱን ግብ በተለይም የ2063 አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በሥራ ዘመን ቆይታቸው 55ቱን የአፍሪካ ሀገራት መጎብኘት እንደቻሉ የገለጹት ሊቀመንበሩ ይህም የአፍሪካን ታሪክ፣ እምቅ አቅም እንዲሁም ማነቆ የሆኑባትን ጉዳዮች እንድመለከት አስችሎኛል ብለዋል።

ያለፉት ዓመታት አፍሪካ ዓለም አቀፋዊ በኾኑ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች እንደተፈተነችም አስታውሰዋል።

በአባል ሀገራቱ ያሉ ግጭት እና ያለመስማማቶች፤ በምግብ ዋስትና፣ በሰላም እና ፀጥታ እንዲሁም ተለዋዋጭ ጉዳዮ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ አመላካች መኾናቸውን ጠቁመዋል።

ተሰናባቹ ሊቀመንበሩ አክለውም “በሥራ ዘመኔ ማጠናቀቂያ የማስተላልፈው የመጨረሻ መልዕክት በመሆኑ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማኛል” ሲሉ ገልፀዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና የማግኘት ጥያቄ የክፍለ ዘመኑ ፍትሐዊ ጥያቄ ነው” ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
Next articleየ2025 የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበርነትን አንጎላ ተረክባለች።