
ደሴ: የካቲት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለ5ኛ ዙር 998 ተማሪዎችን አስመርቋል።
ዛሬ የተመረቁ እና አሚኮ ያነጋገራቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ለትምህርታቸው ትኩረት በመስጠታቸው ውጤታማ መኾናቸውን ተናግረዋል።
በቆይታቸው የቀሰሙትን ዕውቀት በሥራ ዓለም ማኅበረሰቡን በማገልገል እንደሚተገብሩትም ቃል ገብተዋል።
የመቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ካሳ ሻወል (ዶ.ር) ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመቋቋም ለዚህ ምረቃ በመድረሳቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ትምህርት ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እና ለሀገር ዕድገት ያለው ድርሻ ከፍተኛ እንደኾነ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲው ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
በዕለቱም 998 ተማሪዎች ለ5ኛ ዙር መመረቃቸውን ጠቅሰዋል።
ጥራት እና ተደራሽነትን በማጠናከር ዩኒቨርሲቲው ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች የተማሩትን እና የቀሰሙትን ዕውቀት ተጠቅመው ሀገርን እና ማኅበረስብን በታማኝነት እንዲያገለግሉም አደራ ብለዋል።
የመማር ማስተማር ሥራን ለማሳለጥ ሰላም ወሳኝ በመኾኑ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ሁሉም የሰላም አምባሳደር እንዲኾንም ጠይቀዋል
ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!