
ባሕር ዳር: የካቲት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለሁለት ቀናት የሚቆየው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ሲጀመር ቀደም ሲል በተጠናቀቀው የሚንስትሮች ጉባኤ ላይ ተመስርቶ ይካሄዳል።
በስኬት እንደተጠናቀቀ የተገለጸው የሚንስትሮች ጉባኤ ለውይይት የሚሆኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በመለየት ለመሪዎች እንዲቀርብ ይደረጋል።
በዘንድሮው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ መሪዎች ዓለም አቀፋዊ እና አሕጉራዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ኅብረት ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ የማካካሻ ፍትሕ፣ አሕጉራዊ ሰላም እና ደህንነት ውይይት የሚደረግባቸው አጀንዳዎች እንደኾኑ ተጠቁሟል፡፡
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፈጻጸም እና አሕጉራዊ የንግድ እና ኢኮኖሚ ትስስር፣ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ ሥርዓተ ጾታ እና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማት አደረጃጀቶች ላይም ጉባኤው ይወያያል።
አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ለማግኘት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተም ኅብረቱ የሚወያይበት እንደሚኾን ይፋ ተደርጓል።
የሥራ ዘመናቸውን በጨረሱት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ቦታ የአዲስ ኮሚሽነር ምርጫ ማካሄድም ከዚህ ጉባኤ የሚጠበቅ ይኾናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!