የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ እና ነገ ይካሄዳል

14

ባሕር ዳር: የካቲት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያን እና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሃሳብ 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ እና ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባኤው ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ኀላፊዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጉባኤው በተለያዩ አሕጉራዊ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎም ይጠበቃል።

የአፍሪካ ኅብረት ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ የማካካሻ ፍትሕ፣ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ለማግኘት እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች፣ አሕጉራዊ ሰላም እና ደህንነት አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና አፈጻጸም እና አሕጉራዊ የንግድና ኢኮኖሚ ትስስር፣ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ ሥርዓተ ጾታ እና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማት አደረጃጀቶች ላይ ጉባኤው ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
የካቲት 5 እና 6/2017 ዓ.ም የተካሄደው 46ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ መሪዎቹ የሚወያዩባቸውን አጀንዳዎች ማጽደቁም ይታወሳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ አዲስ አበባ ገቡ።
Next articleየአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎች