
ባሕር ዳር: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብድልመጂድ ቴቡኔን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ዛሬ የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብድልመጂድ ቴቡኔን ለሁለትዮሽ ውይይት አግኝቻለሁ። ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በታሪካዊ ትስስር፣ በፓን አፍሪካኒዝም እና በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ቁርኝት ይጋራሉ” ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!