ምክር ቤቱ የዳኞችን ሹመት አጸደቀ።

115

ባሕር ዳር: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ4ኛ ቀን ቀጥሏል።

ምክር ቤቱ በአራተኛ ቀን ጉባኤው የፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።

ምክር ቤቱ ሹመታቸውን ያጸደቀው የፍርድ ቤት ዳኞች፦
👉9 ዳኞች ለጠቅላይ ፍርድ ቤት
👉 3 ዳኞች ለከፍተኛ ፍርድ ቤቶች
ፕሬዝዳንት
👉46 ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች
👉171 ዳኞች ለወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ናቸው።

ምክር ቤቱ ከባድ የሥነ ምግባር ጥሰት የፈጸሙ ሁለት ዳኞችን ለሦስት ዓመታት ከሥራ አግዷል።

ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ለአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ አዲስ አበባ ገቡ።
Next articleየአማራ ክልል ምክር ቤት የቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ።