
አዲስ አበባ: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 38ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገር መሪዎች ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡ የተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም አቀባበል በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
38ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤን ለመሳተፍም የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኦሊድ ጊዞኒ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኦሊድ ጊዞኒም ለተደረገላቸው አቀባበል ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!