የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የአራተኛ ቀን ውሎውን ጀምሯል።

74

ባሕር ዳር: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የአራተኛ ቀን የጉባኤ ውሎን ጀምሯል።

ጉባኤው በአራተኛ ቀን ውሎው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ ያጸድቃቸዋል ተብሎ የሚጠበቁ ረቂቅ አዋጆች፦
👉 የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ ረቂቅ አዋጅ፣
👉 የአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
👉 የአማራ ክልል ፍትሕ እና የሕግ ኢንስቲትዩት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ፣
👉 የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ናቸው።
ምክር ቤቱ በአራተኛ ቀን ውሎው የፍርድ ቤት የዳኞችን ሹመት እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኮሞሮስ እና ናይጄሪያ ፕሬዝዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ
Next article“የተዋሃደች አፍሪካ በዕድል አትፈጠርም” የአፍሪካ ልማት ባንክ