የኮሞሮስ እና ናይጄሪያ ፕሬዝዳንቶች አዲስ አበባ ገቡ

54

ባሕር ዳር: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ እና የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ አሕመድ ቲኒቡ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ አሕመድ ቲኒቡ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የመሪች ጉባዔ የካቲት 8 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየግብጽ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ።
Next articleየአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የአራተኛ ቀን ውሎውን ጀምሯል።