
ባሕር ዳር: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በሦስተኛ ቀን ውሎው የቀረቡለትን ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም ረቂቅ አዋጆችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ሪቂቅ አዋጆችን ማውጣት እና ማሻሻል የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያስችል ተናግረዋል። የፍትሕ ሥርዓቱን ውጤታማ በማድረግ ለዜጎች ፍትሕን መስጠት እንደሚገባም ተናግረዋል።
በአዋጆች ላይ ሰፊ ውይይት እንደተደረገባቸውም ገልጸዋል። ረቂቅ አዋጆችን ማዘጋጀት እና ማሻሻል ዘመኑን የዋጀ እና የሕዝብን ጥቅም ያስከበረ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ነው ያሉት።
ረቂቅ አዋጆችን ማዘጋጀት እና ደንቦችን ማሻሻል መንግሥት ተገቢውን አገልግሎት እንዲሠጥ እና የሕዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እንደሚያስችልም አንስተዋል።
ምክር ቤቱም የቀረቡለትን ረቂቅ አዋጆች መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽቋቸዋል።
ምክር ቤቱ መርምሮ ያጸደቃቸው አዋጆች:-
👉 የአማራ ክልል የመንግሥት አሥተዳደር ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ፣
👉 የጠበቆች አሥተዳደር እና ፈቃድ አሰጣጥ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣
👉 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ናቸው
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!