የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ።

31

አዲስ አበባ: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በምታስተናግደው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም ነው የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ኢትዮጵያ የገቡት።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ.ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ለተደረገላቸው አቀባበልም ምሥጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትላይ አዲስ አበባ ገቡ።
Next articleየኦዲት ግኝቶችን ርምጃ አወሳሰድ እና ማሻሻያ ትግበራን ለማጠናከር ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ ይገባል።