የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትላይ አዲስ አበባ ገቡ።

45

አዲስ አበባ: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በምታስተናግደው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም ነው የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ወደ ምድረ ቀደምቷ ሀገር ኢትዮጵያ የገቡት:: ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል::

የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልም ምሥጋና አቅርበዋል::

ዘጋቢ:- ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሚሰጠው የአየር ንብረት ቅድመ ትንበያ እና ማስጠንቀቂያ መረጃ ተቋማትን እያገዘ ነው” የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Next articleየኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ።