የዓለም ጤና ድርጅት ያልተረጋገጡ መድኃኒቶችን መጠቀም እንደማይገባ አስጠነቀቀ፡፡

151

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ያልተረጋገጡ የባህል መድኃኒቶችን መጠቀም ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ አስጠንቅቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ የባህል መድኃኒቶች ኮሮናን ለመከላከል ጥቅም ላይ እየዋሉ እንደሆነ የማዳጋስከር ፕሬዝዳንት ያስተዋወቁትን “ባህላዊ የኮሮና መከላከያ” የተባለ መጠጥ ምሳሌ አድርጎ አንስቷል፡፡ በእርግጥ የማዳጋስከር ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሬዝዳንቱ ያስተዋዎቁት ባህላዊ መድኃኒት ወደ 20 በሚጠጉ ሰዎች ከ21 ቀናት በላይ መሞከሩን ገልጸዋል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትን መመዘኛ የሚያሟላ እንደሆነም ይከራከራሉ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ‘‘አፍሪካውያን መጠቀም ያለባቸው በዓለማቀፍ ደረጃ የተረጋገጡ መድኃኒቶችን ነው፤ በባህላዊ መንገድ የሚዘጋጁ መድኃኒቶችም ቢሆኑ ፍቱንነታቸውና ደኅንነታቸው በትክክለኛ ሙከራ የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል’’ ብሏል ድርጅቱ በመግለጫው፡፡ በእርግጥ የዓለም ጤና ድርጅት የሚለው ‘ክሊኒካል ሙከራ’ ረዥም ጊዜ ወሳጅና አራት ደረጃዎች ያሉት መድኃኒት ወይም ክትባት የማምረት ሂደት ነው፡፡ የሙከራ ሂደቶቹም ከጥቂት ሰዎች አንስቶ ሀገራዊ ሕዝብን እስከ ማሳተፍ የሚደርሱ ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

በአብሃም በዕውቀት

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዮቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleባለፉት 24 ሰዓታት በ17 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
Next article‘‘ለሕገ ወጥ የሰዎች ደላላ ምንም ዓይነት ምሕረት አያስፈልግም፤ ይህ አገርን እንደማጥቃት ይቆጠራል።” ዶክተር ስዩም መስፍን