“የሚሰጠው የአየር ንብረት ቅድመ ትንበያ እና ማስጠንቀቂያ መረጃ ተቋማትን እያገዘ ነው” የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

18

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የምዕራብ አማራ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ለባለ ድርሻ አካላት የግንዛቤ ፈጠራ እና 2017 ዓ.ም የበልግ ወቅታዊ የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የሪሞት ሴንሲንግ እና ክላይሜት ተመራማሪ ዘላለም ዓለማየሁ የግንዛቤ ፈጠራ ፎረሙ የአየር ንብረት ቅድመ ትንበያ እና ማስጠንቀቂያ ላይ ተዓማኒ መረጃ ለመስጠት ያስችላል ነው ያሉት።

የሚገኘው መረጃም ለተለያዩ ምርምሮች እና የአየር ንብረት ለውጥን ለማጥናት ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል። በተለይም መረጃውን የእርሻ፣ የውኃ፣ የአቬሽን፣ የቱሪዝም እና የትምህርት ተቋማት በአግባቡ ከሚጠቀሙበት መካከል ይጠቀሳሉ።

ቅድመ ትንበያ እና ማስጠንቀቂያ መረጃ የሰውን ሕይዎት እና ንብረት በመታደግ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መኾኑንም ተመራማሪው ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ሙሉጌታ ሙጨ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቅመው ራሳቸውን ለመለወጥ ዝግጁ እንደኾኑ ተፈናቃዮች ተናገሩ።
Next articleየባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትላይ አዲስ አበባ ገቡ።