በብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አባንግ ኩሙዳን የተመራ ልዑክ በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረገ ነው።

63

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የጽሕፈት ቤት ኀላፊ አባንግ ኩሙዳን የተመራ ልዑክ በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረገ ነው።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ለልዑካን ቡድኑ የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ልዑኩ በቆይታው ሀገራዊ የወጣቶች የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሀብት እና የማኅበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ለማጎልበት በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት በወጣቶች ክንፍ የተሠሩ ሥራዎች፣ ስኬቶች እና ጉድለቶችን ይገመግማል። የቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚያስቀምጥም ይጠበቃል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ መሪዎች ፣ የሁሉም የክልል እና የከተማ አሥተዳደሮች የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች ይሳተፋሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደብረ ታቦር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን በ2018 ዓ.ም ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
Next articleንጋት ኮርፖሬት ከ1 ነጥብ 792 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።