
ባሕር ዳር: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቴንዮ ጉተሬዝ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ በምታስተናግደው 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም፣ እንኳን ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እና ውቧ የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በደህና መጡ ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!