የአማራ ክልል ምክር ቤት ሦስተኛ ቀን የጉባኤ ውሎውን ማካሄድ ጀምሯል።

76

ባሕር ዳር: የካቲት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦሰተኛ ቀን ጉባዔውን ጀምሯል። ዛሬ በሚኖረው የጉባኤ ውሎ በቀዳሚነት ንጋት ኮርፖሬት ያቀረበው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በመቀጠልም የተለያዩ ረቂቅ አዋጅ እና ደንቦችን ተመልክቶ ከተወያየ በኃላ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ዛሬ ለምክር ቤቱ ከሚቀርቡ አዋጆች እና ደንቦች መካከል:-

👉 የአማራ ክልል መንግሥት የአሥተዳደር ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የጠበቆች አሥተዳደርና ፈቃድ አሰጣጥ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የተሻሻለው የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የአማራ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ማጠናከሪያ ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋም እና እውቅና ለመስጠት የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የአማራ ክልል ፍትሕ እና የሕግ ኢንስቲትዩት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ፣

👉 የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብ ይገኙበታል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከቱኒዚያ እና ሞሮኮ አቻወቻቸው ጋር ተወያዩ።
Next article“እንኳን ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ በደህና መጡ” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ