የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከቱኒዚያ እና ሞሮኮ አቻወቻቸው ጋር ተወያዩ።

28

ባሕር ዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከቱኒዚያ እና ሞሮኮ አቻወቻቸው ጋር ተወያይተዋል።

ዛሬ ከተጀመረው 46ኛው የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ.ር) ከቱኒዚያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ አሊ ናፍቲ ጋር ተወያይተዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች አሁን ላይ ያለውን የሁለቱ ሀገራትን ግንኙነት የበለጠ በማሳደግ በንግድ ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም ፣ ኢነርጂ፣ አይሲቲ እና ትምህርት መስኮች በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው መስኮች ዙሪያ መክረዋል።

የጋራ የሚነስትሮች ስብሰባ በቅርቡ ለማካሄድ እና በአህጉሪቱ ሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡሪታ ጋር ተወያይተዋል። የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ሚኒስትሮቹ ይኸንን ተግባራዊ ለማድረግ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ማድረግ እንደሚገባ ተግባብተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአፍሪካ ደረጃ ተምሳሌት የሚኾን የግልግል ዳኝነት ማዕከል የግንባታ ሂደት ተጀምሯል” የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
Next articleየአማራ ክልል ምክር ቤት ሦስተኛ ቀን የጉባኤ ውሎውን ማካሄድ ጀምሯል።