
ደብረ ማርቆስ: የካቲት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎችን በሚመለከት በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከመምሪያ እስከ ቀበሌ ከሚገኙ መሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ መሪዎች በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና በተቀመጡ አቅጣጫዎች ተፈጻሚነት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በመድረኩ መክፈቻ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው በጉባኤው የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በሚገባ ተገንዝቦ ወደ ታች በማውረድ ወደተግባር እንዲቀየሩ መሪዎች የድርሻቸውን መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
ጠንካራ መሪ በመኾን የፓርቲው ውሳኔዎች እና ሀገራዊ ተልዕኮዎች በላቀ ደረጃ እንዲፈጸሙ መሪዎች ኀላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት አለባቸው ነው ያሉት፡፡
የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በየዘርፉ ከታቀዱ የአጭር እና የረጅም ጊዜ እቅዶች ጋር አዋሕዶ በመፈጸም የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመፍታት በጋራ መረባረብ እንደሚገባም ኀላፊው አሳስበዋል፡፡
በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የተላለፉ አቅጣጫዎችን እንደየ ዘርፋቸው ወደ ተግባር በመለወጥ እና ማኅበረሰቡን በማሳተፍ ሕዝብ እና መንግሥት የሰጣቸውን ኀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውን የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!