
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና የከተማ ነዋሪዎች ደም ለግሰዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ወንድወሰን ሞላ እንደተናሩት መምህራንን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና የከተማ ነዋሪዎችን በማስተባበር “ሳልዘናጋ ከኮሮና እጠነቀቃለሁ ደሜን ለወገኔ እሰጣለሁ” በሚል መሪ ሐሳብ ከሚያዚያ 26 እስከ 27/ 2012 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሀ ግብር መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ ለሁለት ቀናት በተደረገው የደም ልገሳ መርሀ ግብርም 107 ሰው ደም መለገሱን ተናግረዋል፡፡
ደም ከለገሱ ግለሰቦች መካከል አቶ እርቂሁን ዓለሙ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተከሰተውን የደም እጥረት ለመቅረፍ የመፍትሔ አካል ለመሆን ደም መለገሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ዛሬ የሚሰበሰበው ደም ነገ ለቤተሰቡ መልሶ የሚያገለግል በመሆኑ ማኅብረሰቡ ደም ሳይሳሳ መለገስ እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው መምህር እና የደም ልገሳው አስተባባሪ አቶ ዮናስ ደርበው ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከተደረገው የደም ልገሳ ፕሮግራም በተጨማሪ በሌሎች ከተሞችም ደም የመሰብስብ ሥራ እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡ ዛሬም በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ደም የመሰብሰብ ሥራ እየተሠራ እንደሆነ በአብነት ጠቅሰዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዮቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡