በሁሉም ዘርፍ ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥራ እንደሚሠሩ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር መሪዎች ገለጹ፡፡

53

ደሴ: የካቲት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የድህረ ጉባኤ ውሳኔዎች ላይ ከክፍለ ከተማ እና መምሪያ ኀላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ለውጦችን መነሻ በማድረግ በቀጣይ በሁሉም ዘርፍ ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤት ለማምጣት የሚያስችል ግንዛቤ የጨበጡበት እንደኾነ ተናግረዋል።ውጤታማ ሥራ እንደሚሠሩም አመላክተዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉጌታ አቢ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በተላለፉ ውሳኔዎች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለጠቅላላ መሪዎች ግልጽ የማድረግ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል።

ባለፈው ሁለት ዓመት ተኩል ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት በከተማዋ በርካታ የልማት፣ የመልካም አሥተዳደር እና የሰላም ጉዳዮች መከናወናቸውንም አንስተዋል።

በቀጣይም ጠንካራ ፓርቲ ግንባታን አጠናክሮ መቀጠል፣ ብሔራዊና ገዥ ትርክት ግንባታን ማጠናከር፣ ውጤታማ የሰላም ግንባታ ሥራ መሥራት፣ የፍትሕ ዘርፍ ውጤታማነትን ማሳደግ፣ የሀገር ግንባታን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ልማትን ማፋጠን፣ ማኅበራዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በውጤታማነት ማስቀጠል፣ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን መሥራት፣ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ውጤታማነትን ማረጋገጥ፣ ጠንካራ የሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ መሥራት የሚሉትን እሳቤዎች በአባላት እና በመላው ማኅበረሰብ ዘንድ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ይደረጋል ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ አንተነህ ፀጋዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምርታማነትን ለማሳደግ የመስኖ አውታሮችን በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በመረጃ መደገፍ ይገባል” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next article“አሁን የተገኘውን ሰላም በማጽናት በአጭር ጊዜ ውስጥ ደግሞ አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በቁርጠኝነት ይሠራል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ