ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለምክር ቤቱ ስለ በግብርናዎው ክፍለ ኢኮኖሚ ካነሷቸው አንኳር ጉዳዮች በጥቂቱ፡-

50

ባሕር ዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው። ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ባቀረቡት የስድስት ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ፦

👉 የግብርናው ዘርፍ ለክልሉ አጠቃላይ ኢኮኖሚ በዓመት በአማካይ 168 ቢሊዮን ብር እያበረከተ ይገኛል።

👉 ከክልሉ ኢኮኖሚ በአማካይ እስከ 37 ነጥብ 3 በመቶ የሚኾነውን የሰብል ምርት ይሸፍናል።

👉 ግብርና ለክልሉ ኢኮኖሚ 51 ነጥብ 9 በመቶ የሚኾነውን ድርሻ ይይዛል።

👉 ክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የእንስሳት ሀብት ባለቤት ሲኾን ከክልሉ ኢኮኖሚ 13 ነጥብ 8 በመቶ ያበረክታል።

👉 በየዓመቱ በአማካይ ከ41 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ከእንስሳት ሃብት ይገኛል።

👉 የእንስሳት ሃብት ከክልሉ ኢኮኖሚ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

👉 በአሁኑ ወቅት በክልሉ በ8 ሺህ 844 ተፋሰሶች ላይ የተፈጥሮ ሃብት ሥራዎች እየተሠሩ ናቸው።

👉 የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ባለፉት 6 ወራት 482 የምርምር ሥራዎችን አከናውኗል።

👉 ባለፉት 6 ወራት ወደ 158 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በመመደብ በ22 ወረዳዎች የጎርፍ መከላከል ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው።

👉 በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ለ1 ሚሊዮን 183 ሺህ 18 ተጠቃሚዎች በመንግሥት እና በለጋሽ ድርጅቶች ጥምረት 500 ሺህ ኩንታል በላይ የዕለት ምግብ ድጋፍ ተደርጓል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲመዘገብ እየሠራ መኾኑን የባሕር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ ገለጸ።
Next articleከብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ሳያገኙ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ድሮን በሚያስነሱና በሚያበሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መኾኑ ተገለጸ፡፡