
ባሕር ዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም(አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2017 የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው።
በግምገማው የመምሪያው ከፍተኛ የትምህርት መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች እየተሳተፉ ነው።
በባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ የፈተና ዝግጅት እና አሥተዳደር ባለሙያ አበበ አያሌው በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7ሺህ በላይ የ6ኛ እና ከ8ሺህ በላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲመዘገብ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ከ6ሺህ 504 በላይ ተማሪዎች መካከል 35 በመቶ የሚኾኑት ከ50 በመቶ በላይ ውጤት አምጥተው ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!