
ባሕር ዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም(አሚኮ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ በአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል:-
👉 አምስት አዳዲስ እና ዘመናዊ ሆስፒታሎች እስከ ሰኔ 30/2017ዓ.ም ድረስ ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት ይገባሉ።
👉 በጸጥታ ችግር የተጎዱ 27 ሆስፒታሎች እና 45 ጤና ጣቢያዎች እየተጠገኑ ነው።
👉 ደረጃቸውን የማይመጥን ግንባታ ያላቸው 6 አጠቃላይ ሆስፒታሎች ተጨማሪ ግንባታ እየተደረገላቸው ነው።
👉117 ጤና ጣቢያዎች ላይ የመለስተኛ ቀዶ ጥገና ክፍል ተገንብቶላቸዋል፤ ከዚህ ውስጥ 107 የሚኾኑት ተጠናቅቀዋል።
👉 155 ጤና ጣቢያዎች ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ የአልትራ ሳውንድ ምርመራ ተጀምሯል።
👉 ከታቀደው ሕዝብ ውስጥ እስካሁን ድረስ 39 በመቶ የሚኾነው የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድኅን አባል ኾኗል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!