የወደሙ የውኃ መሠረተ ልማቶች ተመልሰው እየተገነቡ መኾኑን የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ገለጸ።

31

ባሕር ዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም(አሚኮ) በጸጥታ ችግር ምክንያት የወደሙ የውኃ መሠረተ ልማቶች ተመልሰው እየተገነቡ መኾኑን የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ገልጿል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው። በጉባዔው የምክር ቤት አባላት በየአካባቢው የተጀመሩ የንጹሕ መጠጥ ውኃ አገልግሎት ፕሮጀክቶች በጊዜ እንዲጠናቀቁ ጠይቀዋል።

ለጥያቄዎች መልስ እና ማብራሪያ የሰጡት የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር) የክልሉን የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ሽፋን ለማሳደግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል። ቢሮው በራሱ ባለሙያዎች እና በራሱ አቅም የውኃ ፕሮጀክቶችን እየገነባ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

ከፌዴራል መንግሥት ጋር በጋራ በመኾን ዘርፉ የበለጠ እንዲያድግ እየሠራን ነው ብለዋል። ያልተጠናቀቁ የውኃ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ እና አዳዲስ ሥራዎችም እንዲጀመሩ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራም ተናግረዋል።

ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ በክልሉ የነበረው የጸጥታ ችግር በውኃ መሠረተ ልማቶች ላይ ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል።

የወደሙ የውኃ መሠረተ ልማቶች ተመልሰው እንዲገነቡ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱንም ተናግረዋል። በተደረገው ጠንካራ ጥረት የዘርፉን መሠረተ ልማቶች መልሶ መገንባት መቻሉንም ጠቅሰዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የቆዬ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሠሩ አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ።
Next article“በክልሉ በጀት የሚሠሩ 189 የመንገድ ፕሮጀክቶች በዚህ ዓመት ይጠናቀቃሉ” የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ