የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የቆዬ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሠሩ አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ።

32

ባሕርዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ለፕሮቶኮል ተጠባባቂ ሹም አቢ ጆንስ አቅርበዋል።

አምባሳደሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት መኖሩን ተናግረዋል። በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኢምባሲ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ለፕሮቶኮል ተጠባባቂ ሹም አቢ ጆንስ አምባሳደሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሚያከናውኑት ተግባራት አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንደሚያደርጉላቸው ቃል ገብተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት የሁለተኛ ቀን ውሎ ጉባኤውን ጀምሯል።
Next articleየወደሙ የውኃ መሠረተ ልማቶች ተመልሰው እየተገነቡ መኾኑን የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ገለጸ።