የአማራ ክልል ምክር ቤት የሁለተኛ ቀን ውሎ ጉባኤውን ጀምሯል።

30

ባሕር ዳር: የካቲት 05/2017 ዓ.ም(አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4 ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባዔ የሁለተኛ ቀን ውሎ ጉባኤውን ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው ትናንት በቀረበው የክልሉ መንግሥት የስድስት ወራት የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በመቀጠልም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2017 በጀት ዓመት ሁለተኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን አዳምጦ በመወያየት እንደሚያጸድቅም ይታሰባል።

በተጨማሪም ንጋት ኮርፖሬት ያከናወናቸውን የልማት ሥራዎች የተመለከተ ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርቦ ከተወያየ በኋላ ማጽደቅም በዛሬ የምክር ቤቱ የጉባኤ ውሎ የሚጠበቁ ተግባራት ናቸው።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article19 ዘመናዊ የመስኖ ፕሮጄክቶች እየተገነቡ መኾናቸውን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገለጸ።
Next articleየኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የቆዬ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሠሩ አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ።