“ከ3 ሚሊዮን 112 ሺህ በላይ ሰዎች የወባ በሽታ ምርመራ አገልግሎት አግኝተዋል” ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ

31

ባሕር ዳር: የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4 ዓመት የሥራ ዘመን፣ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የ6 ወራት የልማት እና የመልካም አሥተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ የጤናው ዘርፍ ሥራዎችን አፈጻጸም አቅርበዋል።

በዚህም መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት፦

👉 ከ1 ነጥብ 56 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የሕክምና ቁሳቁስ ተሰራጭቷል፤

👉 334 የጤና ዘርፍ የግንባታ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው። ከዚህ ውስጥ 24 የሚኾኑት ተጠናቅቀዋል፤ ቀሪዎችም በፍጥነት እየተከናወኑ ነው።

👉 344 ሺህ 969 ሕጻናት ሁሉንም ዓይነት ክትባት አግኝተዋል፤ ይህም ከዕቅዱ አኳያ 94 በመቶውን የሸፈነ ነው።

👉 ከ3 ሚሊየን 112 ሺህ በላይ ሰዎች የወባ በሽታ የጥርጣሬ ምርመራ የተደረገላቸው ሲኾን በበሽታው ተጠቅተው የተገኙትም አስፈላጊውን ሕክምና አግኝተዋል።

👉 262 ሺህ 350 እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት ያገኙ ሲኾን ይህም ከእቅዱ አኳያ 66 በመቶ የሸፈነ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከ10 ሚሊዮን በላይ የአዲሱ የሥርዓተ ትምህርት መጽሐፍት ታትሟል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“በኮሪደር ልማቱ ማኅበረሰቡ ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል” አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ