
ባሕር ዳር: የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች በተገኙበት በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የሚመክር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን ውይይቱ መሪዎች እና አባላት በአጀንዳዎቹ ዙሪያ የጠራ አቋም በመያዝ የተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ዕውቅና እንዲኖራቸው፣ የቀጣይ አቅጣጫዎችን የጋራ በማድረግ የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በፈተናዎች ሳይበገር በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል። ” የተገኙ ለውጦችን ማስቀጠል እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ ለሕዝብ ተጠቃሚነት እና ለሀገር ብልጽግና መሥራት እንደሚገባ” አመላክተዋል።
ከደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደበበ አክሎግ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎችን እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!