የተቀመጡ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎችን አሟልቶ በመተግበር ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።

26

ባሕር ዳር: የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ”ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት ከከተማ፣ ከክፍለ ከተማ እና ከቀበሌ መሪዎች ጋር የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ማድረግ ጀምሯል።

በብልጽግና ፓርቲ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞላ ሁሴን የፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ በቅርቡ መደረጉን አስታውሰው በጉባኤውም በአንደኛው መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን እና የተቀመጡ አቅጣጫዎች እንደተገመገመ ጠቁመዋል። ያጋጠሙ ፈተናዎችንም በማለፍ ዕቅዶችን በመተግበር እና ልማት በማምጣት የመጣው ለውጥ ቀላል እንዳልኾነ መገምገሙን አንስተዋል።

አቶ ሞላ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤም ውሳኔዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ተናግረዋል። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከየደረጃው አመራር ጋር ውይይት የማድረጉ ዓላማም በብልጽግና ጉባኤ የተወሰኑ ውሳኔዎችን፣ የተሰጡ አቅጣጫዎችን መሪዎች የሚገነዘቡበትን መንገድ እና አተገባበራቸውን ተወያይቶ የጋራ ለማድረግ መኾኑን ተናግረዋል።

ውይይቱ በመሪዎች ብቻ የሚወሰን ሳይኾን በብልጽግና ቤተሰብ እና ኅብረት እንዲሁም ሁሉም በየደረጃው ያለ ማኅበረሰብ ድረስ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በየደረጃው የሚደረገውን ውይይት በአግባቡ ለመምራት እና ውጤታማ ለማድረግ የዛሬው ውይይት በትኩረት የሚፈጸም ይኾናል ብለዋል።

ከፓርቲው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች በተጨማሪም ባለፉት ስድስት ወራት በከተማው የተከናወኑ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር፣ የሰላም እና ጸጥታ ማስከበር ሥራዎች ምን ደረጃ ላይ እንደደረሱ እንዲሁም በቀጣይ ጊዜ ሥራዎች ላይም ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎችን በተሟላ ሁኔታ በማስገንዘብ እና በመተግበር ኅብረተሰቡን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- ዋሴ ባየ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እንኳን ወደ ቤታችሁ በደህና መጣችሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleአቶ አደም ፋራህ በዓለም የመንግሥታት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው።