“እንኳን ወደ ቤታችሁ በደህና መጣችሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

73

ባሕር ዳር: የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ለሚገቡ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ የምትሳትፉ እንግዶች የቆይታ ጊዜያችሁን እንድታራዝሙ እመክራለሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያ እውነተኛዋ ምድረ ቀደምት ሀገር እንደኾነች የሚያሳዩ የዳበረ ታሪክ፣ ፣ ልዩ ልዩ ባሕሎች እና አስደናቂ መልክዓ ምድሮች እንድትመለከቱ አበረታታለሁ ብለዋል።

ከጉባኤው ባሻገር ከጥንታዊ ቅርሶች እስከ ደማቅ ወጎች እና ወደር የለሽ የተፈጥሮ ውበቶች መኖራቸውን አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር እንኳን ወደ ቤታችሁ በደህና መጣችሁ ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የልጆች ከትምህርት ገበታ ማቋረጥ ወላጅ የኾነን ሁሉ ሊያሳስብ ይገባል” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleየተቀመጡ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫዎችን አሟልቶ በመተግበር ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።