
ባሕር ዳር: የካቲት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ”ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት ከከተማ፣ ከክፍለ ከተማ እና ከቀበሌ መሪዎች ጋር በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫወች ላይ ውይይት ማድረግ ጀምሯል።
በውይይቱ ገዥው ፓርቲ በጉባኤው የገመገማቸውን ያለፉ ዓመታት ክንውኖች፣ ያስቀመጣቸውን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት እስከ ኅብረተሰቡ ለማድረስ በሚቻልባቸው አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!