የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ።

49

ባሕር ዳር: የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው ከየካቲት 04 እስከ 07/2017 ለአራት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል። በቆይታውም በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ የክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የልማት እና የመልካም አሥተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያዳምጣል። የቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል።

ምክር ቤቱ በጉባኤው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የክልሉ ዋና ኦዲተር የስድስት ወራት ሥራ አፈጻጸም ላይ እንደሚመከርም ተገልጿል።

ምክር ቤቱ የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል። በጉባኤው የመጨረሻ ቀን ውሎም የፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት ያፀድቃል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕዝቡን ሰላም እና ደኅንነት ለመጠበቅ ጠንካራ ሥራ መሠራቱን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ገለጸ።
Next articleየባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ በገዥው ፓርቲ የጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ እየመከረ ነው።