በቀጣይ ሦስት ዓመታት ለ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ገለጸ።

30

ባሕር ዳር: የካቲት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) እንዳሉት ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከታቀደው 4 ነጥብ 89 ሚሊዮን ዜጎች ውስጥ 81 በመቶ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። ከዚህ ውስጥ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚኾኑት በቋሚነት የተፈጠረላቸው ናቸው ነው ያሉት።

የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ውስጥ ደግሞ ለ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ወጣቶች በግብርና፣ ለ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ወጣቶች በኢንዱስትሪ እና ለ1 ሚሊዮን የሚኾኑት ወጣቶች ደግሞ በአገልግሎት ዘርፍ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ናቸው። ከሀገር ውስጥ ባለፈ ለ110 ሺህ ለሚኾኑ ዜጎች በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

በቀጣይ ሦስት ዓመታት እንደ ሀገር ለ9 ነጥብ 15 ፣ በአማራ ክልል ደግሞ ለ3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅጣጫ መቀመጡን ነው ኀላፊው የገለጹት። የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪትም ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መኾኑን ያነሱት ኀላፊው ወጣቶች በሥራ እና ሥልጠና ማዕከላት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲኾኑ አሳስበዋል።

በክልሉ የተከሰተው የጸጥታ ችግር የተሠራጨውን ብድር ለማስመለስ፣ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እና ድጋፍ እና ክትትል ለማድረግ ፈተና መኾኑንም አንስተዋል የታቀደውን ዕቅድ ለማሳካት ክልሉ ያለውን ጸጋ በአግባቡ መጠቀም ይገባልም ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በማኅበረሰቡ እየደረሰ ላለው የሥነ አዕምሮ ጤና እና የሥነ ልቦና ችግር ትኩረት ማድረግ ይገባል” ታፈረ መላኩ (ዶ.ር)
Next article“ሰላም ከሁሉም ይቀድማል” የደባርቅ ከተማ ሴቶች