
ባሕርዳር: የካቲት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክልል ማዕከል በሆኑ ከተሞች እና በሌሎች የዞን ማዕከላት የኮሪደር ልማት ተጠናክሮ እየተሠራ ነው።
ከፌዴራል፣ ከዞን፣ከከተማ አሥተዳደር እና ከኅብረተሰብ ተሳትፎ በተገኝ ሀብት በስምንት ከተማ አሥተዳደር እየተሠራ ነው ተብሏል።
ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ ካራት እና ይርጋ ጨፌ ከተሞች በኮሪደር ልማት 41 ኪሜ መንገድ፣ 26 ሄክታር የአረንጓዴ ቦታዎች እና የፓርክ ልማት፣ 9 የልጆች መጫወቻ ቦታዎች ፣11 ኪሜ የመንገድ ዳር መብራትና ሕንጻ የማስዋብ ሥራ እና 0.18 ሄክታር የአደባባይ ቦታዎች የማልማት ሥራ 3 ፋውንቴን ሥራዎች ተሠርተዋል ነው የተባለው።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሐፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አንዳንዶች የመጀመሪያ ዙር አጠናቀው ሁለተኛ ዙር ጀምረዋል። አርባምንጭ ከተማ፣ የእግረኛ መንገድ በአንድ በኩል፣ የብስክሌት መንገድ ፣ አረንጓዴ ስፍራ እና የመብራት ስማርት ላይት ያካተተ ሥራ ተከናውኗል ነው የተባለው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!