
ጎንደር: የካቲት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ወጣቶች ለተሐድሶ ሥልጠና ወደ ጠዳ የሥልጠና ማዕከል ገብተዋል። ሠልጣኞቹ ለታጣቂዎች መረጃ በመሥጠት፤ ሎጅስቲክ በማቅረብ እና ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መኾናቸው ተነስቷል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ መኮንን በክልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ማኅበረሰቡ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ እና ወርቶ እንዳይበላ ጫና አሳድሯል ብለዋል።
በመነጋገር እና በመወያየት ችግሮችን ልንፈታ ይገባል ያሉት ኀላፊው ከግጭት ይልቅ የሰላም አማራጭን በመውሰድ ለክልሉ ሰላም ትልቁን ድርሻ ልትወስዱ ይገባል ነው ያሉት።
አንድነትን በማስቀደም አባቶች በመስዋዕትነት ያስረከቡንን ሀገር ሰላምን በማጽናት ለቀጣይ ትውልድ ልታስተላልፉ ይገባል ብለዋል። ሥልጠናውን በትኩረት በመውሰድ ከሥልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ በመጠቀም ስለ ሰላም ሊሠሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!