የአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

87

ባሕር ዳር: የካቲት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን “የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ ለሰላም እና ለዴሞክራሲ” በሚል መሪ መልዕክት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።
በጉባኤው ላይ ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የርዕሰ መሥተዳደሩ የሕዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት አማካሪ ይርጋ ሲሳይ እንዲሁም የሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ጉባኤው ከየካቲት 02 እስከ 05/2017 ዓ.ም ለ4 ቀናት ነው የሚካሄደው።

የፌዴሬሽኑ ተልዕኮ መላው የክልሉ ሴቶች በተለያዩ አደረጃጀቶች በመሳተፍ ለመብቶቻቸው የሚቆሙ፣ በተዘረጋው የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ፖሊሲ ግንዛቤ ኖሯቸው ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማስቻል ነው። ለሴቶች ተግባራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትም ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ይሠራል።
በጉባኤው የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ፣ ሰላም ለሴቶች መብትና ደኅንነት ያለውን ሚና እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ እንዲያገኙ የታየው ቁርጠኝነት ለሌሎች ምሳሌ እንደሚኾን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
Next articleየሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ አሳሰቡ።