በአሁኑ ወቅት የኮሪደር ልማት በአማራ ክልል ሰባት ከተሞች በመስፋፋት ላይ ይግኛል፡፡

81

የኮሪደር ልማት በከተሞቹ የራስ ዐቅም፣ ከሕዝብ ተሳትፎ፣ ከፌዴራልና ከልዩ ልዩ ድጋፎች በሚገኝ ዐቅም እየተተገበረ ነው። በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ እና ወልድያ ከተሞች ተጀምሮ 32 ነጥብ 23 ኪ.ሜ መንገድ 27 ነጥብ 04 ሄክታር አረንጓዴና ፓርክ ልማት፣ 3 ነጥብ 7 ሄክታር የሕዝብ አደባባይ፣ 25 ኪ.ሜ የመንገድ ዳር መብራትና ሕንፃ የማስዋብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ከተለመደዉ የፕሮጀክት አፈጻጸም በተለየ ሁኔታ በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍሎ በአጭር ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እየተተገበረ ነው። ጎንደር፣ ኮምቦልቻና ባሕርዳር ከተሞች የመጀመሪያ ምዕራፍ በማገባደድ ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ ሥራዎች በመሸጋገር ላይ ናቸዉ፡፡
በዚህ የኮሪደር ልማት እንደ ባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ባሉ ከተሞች ግራ እና ቀኝ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገድ፣ ፐብሊክ-ፕላዛ (ማረፊያና መዝናኛ)፣ የመጸዳጃ ቤቶችና ዘመናዊ ካፍቴሪያዎች እየተገነቡ ነው። በግራ እና ቀኝ ከ5 ሜትር በላይ ስፋት ያለዉ አረንጓዴ ልማት ተከናውኗል። የሐይቅ ዳርቻውን ለሕዝብ የመክፈት ሥራ ተሠርቷል።

መረጃው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው

Previous article24 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ በቀዶ ጥገና ማስወገዱን እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል አስታወቀ።
Next articleየመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተሀድሶ ሥልጠና ሲወስዱ ቆይተው ለተመለሱ ሠልጣኞች አቀባበል ተደረገ።