
እንጂባራ: የካቲት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፓዌ ወረዳ የ01 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ትሁን ገነቱ 38 ዓመታቸውና የ3 ልጆች እናት ናቸው። የዘር ፍሬ ማምረቻ አካል ውስጥ በተፈጠረ ግዙፍ ዕጢ ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ ያመሩት እኒህ እናት አንድ ሰዓት ከ45 ደቂቃ በወሰደ ከባድ ቀዶ ጥገና ለዓመታት ከቆየባቸው ከባድ የጤና ችግር ተገላግለዋል።
የቀዶ ጥገና ቡድኑ መሪ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ማርቆስ አዲሱ 24 ኪሎ ግራም የሚመዝነው እጢ ግዙፍ ከመሆኑ የተነሳ የታካሚዋን አተነፋፋስና እንቅስቃሴ በማስተጓጎል ለከፍተኛ የጤና መታወክ ዳርጓቸው መቆየቱን ተናግረዋል። የቀዶ ጥገና ቡድኑ ባደረግው ከባድ ቀዶ ጥገና 24 ኪሎ ግራም የሚመዝን እጢ በማስወገድ ታካሚዋ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ዶክተር ማርቆስ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
