የመጀመሪያው ምዕራፍ የሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ

23

የሀረር ጀጎል የዓለም ቅርስ ከባቢን በማላቅ ለጎብኝዎች እና ለነዋሪዎች እንቅስቃሴ የበለጠ ምቹ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር።

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማቱ ወደ ሁሉም የሀረር ከተማ አካባቢዎች በመስፋት ለወቅታዊ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ ሁናቴ እየተከናወነ ይገኛል። ይህ ሥራ ከፍ ያለ ቁጥር እና መልክ ያላቸው የሥራ እድሎችን ለወጣቶች እና ሴቶች መፍጠር ብቻ ሳይሆን ለቱሪዝም መጨመርም አስተዋፅዖ አድርጓል።

በተጨማሪም የአካባቢው አምራች ኢንዱስትሪዎች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት እንደ ኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በማምረት እና በተለያዩ ጠቃሚ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ ዘላቂ እና ቀጣይነት ያለው እድገትን በማረጋገጥ በጠንካራ የአካባቢው ሕዝብ ተሳትፎ እየተመራ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

Previous articleየሕዝብ ሰላምን ለማወክ ሊውል የነበረ ተተኳሽ ተያዘ።
Next article“የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማፋጠን ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማቶች በስፋት እየተገነቡ ነው” የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር