ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ በረከት ስምዖን የክስ መዝገብ የቅጣት ውሳኔ ለማሳለፍ ለሚያዝያ 30 ቀጠረ፡፡

274

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 28/2012 ዓ.ም (አብመድ) ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ በረከት ስምዖን የክስ መዝገብ የቅጣት ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ባለፈው ችሎት በአቶ በረከት ስምዖን እና በአቶ ታደሰ ካሳ በተወሰኑት የክስ መዝገቦች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላለፈው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ችሎት በሁለቱም ወገን የቀረበውን የቅጣት አስተያዬት ሲያዳምጥ ቆይቷል፡፡

የቅጣት አስተያዬቱን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠትም ለሚያዝያ 30 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዮቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡

Previous articleየደምበጫ ከተማ ነዋሪዎች ደም እየለገሱ ነው፡፡
Next articleየጠረጴዛ እርከን ልማቱ ለሌሎች አካባቢዎች ምሳሌ እንደሚሆን ርእሰ መሥተዳድሩ ገለጹ።